ማቴዎስ ወንጌል 6:19 -21
ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤
ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ።
መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።
ከዚህ ቀጥሎ የምናየው አገልጋይ ታሪክ ይህን ጥቅስ በህይወቱ የተገበረ ነው።
እንደምትባረኩበት አምናለሁ።
እስቲ ስለዚህ አስገራሚና ድንቅ የእግዚአብሔር ሰው ትንሽ ለማየት እንሞክር ።
ስሚዝ ዊገልስዎርዝ (Smith wiggles worth)1859-1947
በ18ኛው ክፍለ ዘመን በፔንቴኮስታል የእምነት ተከታዮች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ያሳደረ ሰው ነበር።
በተለይም በፈውስ
አገልግሎቱ እጅግ ታዋቂ ሰው ለመሆን ችሏል ከዚህም የተነሳ የእምነት ሀዋርያ የሚል ስያሜን አግኝቷል ። ለፔንቴኮስታል
እምነት ፈር ከቀደዱት ውስጥ አንደኛው ነው ቢባል በፍጹም ማጋነን አይሆንም።
በትውልዱ እንግሊዛዊ ነው። ከችግረኛ ቤተሰብ የተወለደ በመሆኑ ገና
ከአፍላ እድሜው ጀምሮ ቤተሰቦቹን በስራ የማገዝ ሃላፊነት ወደቀበት። አባትና እናቱ ቤተሰባቸውን ለመደገፍ የተሰማሩበት ሞያ
በወቅቱ ግብርና ላይ ያተኮረ ነበር። ይሄንንም ስራቸውን ለማከናወን በማለዳ አስራ ሁለት ሰአት ወጥተው ማታ እስከ አስራ ሁለት
ሰአት በስራ ቦታቸው ላይ መቆየት የየዕለቱ ተግባራቸው ሆኖ ነበር። ታዲያ ይሄ አድካሚና አሰልቺ ህይወት የመረረው ስሚዝ እንዲህ ሲል ብሶቱን ይገልፃል።
አስራ ሁለት ሰአት ሙሉ እዚህ ቦታ ላይ መቆየት በጣም ረጅምና አድካሚ ነው።
አባቱም
እንባው ከአይኖቹ እየረገፉ ልጄ ሁሌ አስራ ሁለት ሰአት ደግሞ መድረሱ አይቀርም በማለት ልጁን ለማፅናናት ይሞክራል።
በወቅቱ እናትና አባቱ ከዛ የተሻለ ስራ ለማግኘት ከባድና ቤተሰባቸውንም መመገብ የሚችሉበት ብቸኛ አማራጭ እሱ ብቻ ነበር።
ለስሚዝ ግን የቀኑ ርዝመት አንድ ወር ያህል ሆኖ ይሰማው ነበር።የሁሉም ሰው ዝንባሌ ባይሆንም አንዳንድ የታደለ ሰው ኑሮ ሲመረው ወደፈጣሪው የመቅረብ አቅምና ፍላጎት ያገኛል። ታዲያ በጣም ኑሮ ያስመረረው ስሚዝ በዛ በልጅነት እድሜው ወደ እግዚአብሔር መፍትሔ ፍለጋ መፀለይን አዘወተረ። በድንገት በስራ ቦታ ላይ ሆኖ ተንበርክኮ ይፀልያል ከዛም ከእግዚአብሔር ዘንድ መፅናናትናንና በፊቱ የተጋረጠበትን ችግር የሚቋቋምበትን ጉልበት አግኝቶ ይነሳል ። እግዚአብሔር እንደ ቃሉ ፊቱን
ለሚፈልጉና ለሚጠሩት ሁሉ ይገኝ የለ?? ዘማሪዋ ..."በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ ጌታ መልካም ነው ይሰጣል
እረፍት "...እንዳለችው ...ስሚዝ ሌላ ችግሩን እንዲረሳና ከእግዚአብሔር ጋ በፀሎት ለመገናኘት እድል የከፈተለት
ነገር ተፈጥሮን ማድነቅ ይወዳል። በተለይም ፏፏቴ ያለበት ቦታና የወፎች ዝማሬ የሚሰማበትን ቦታ ያዘወትራል ከዚህም የተነሳ
ረጅም ሰአት በዛ አካባቢ እየተረማመደ በመንፈስ ለመሆንና የውስጥ ሰላምን ለማግኘት ጥሩ አጋጣሚ ሆነለት። ገና ብዙ
የመንፈሳዊነት ሚስጥር ሳይገባው እግዚአብሔርን ማምለክ ግን የህይወቱ ልምምድ አድርጉ ይዞት ነበር።ስሚዝ እንደሚናገረው እናትና አባቱ ክርስቲያን ወይም ሃይማኖተኞች አልነበሩም ነገር ግን የሴት አያቱ የተሰጠች
ሜቶዲስት(Methodist) ቤተክርስቲያን አማኝ ነበረች። ስለዚህ እዛ የመሄድን እድል በሷ በኩል እንዳገኘ ይናገራል ።
ታዲያ አንድ ቀን
በዛ ቤተክርስቲያን የማነቃቂያ ኮንፍረንስ በተደረገበት ቀን የቤተክርስቲያኑ አባላት በደመቀ ዜማ በደስታና በሐሴት ይህን
መዝሙር ..."the lamb the bleeding lamb the lamb of Calvary the lamb…. " እያሉ ሲዘምሩ
ስሚዝ ውስጡ ልዮ ስሜት እንደተሰማውና በህይወቱ ውስጣዊ የሆነ መንፈሳዊ ለውጥ የመጣበት ያ ቀን እንደሆነ ያለ ማመንታት
ይናገራል። ከዛ ጊዜ ጀምሮ የኢየሱስ የመስቀል ስራ በትክክል ትርጉሙን ያወቀበትና የደህንነት ሚስጥር የገባው ቀን ነበር ከዛም
የተነሳ ለነፍሳት የመመስከር ጥማት ከዛች እለት ጀምሮ በውስጡ ይቀጣጠል ጀመር። የመጀመሪያ የጌታን አዳኝነት የመሰከረው ለእናቱ ነበር።
በ16 አመቱ የሳልቬሽን አርሚን ተቀላቀለ በተጨማሪም የቧንቧ ስራ ሙያተኛ ለመሆን መማር ጀመረ። ከዛውጋ
በተጓዳኝ ጌታን የማገልገል በር ተከፈተለት። የጌታን ፊት መፈለግ የሂወቱ ትልቅ ክፍል ስለነበር ጌታን ከማገልገሉ በፊት ለሁለት
ሳምንታት የፆምና የፀሎት ጊዜ ይወስዳል በውስጡ የተጫረው የእግዚአብሔር እሳት ሀይለኛ ነበር።
ስሚዝ ይቺ ቤተክርስቲያን የሳበችው ሀይለኛ የፀሎት አገልግሎትና ነፍሳት በብዛት የሚድኑባት ቦታ መሆኗ ነው። በአንድ ሳምንት ወደ ሃምሳ ሰው ይድን ነበር ይባላል። ስሚዝ ነገርን አዋዝቶ ማቅረብ የማይችል ሀሳቡንም በትክክል ማስረዳት የማይሆንለት
ሰው ነበር ቢባልም ነገር ግን ልክ እንደ ሙሴ ጌታ በሃይለኛው የተጠቀመበት ሰው እንደነበር ይነገርለታል። “ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን
ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ፤ እግዚአብሔር ብርቱዎችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ።”1 ቆሮንቶስ
1:27
ስሚዝ ሳልቬሽን አርሚ ውስጥ እያገለገለ ነው በኋላ ሚስቱ የሆነችውን ፓሊንንም የተዋወቀው። ፖሊን ምክንያቱ ግልፅ
ሆኖ ባይነገርም ግን ከቤተሰቦቿ ቤት ጠፍታ በሰው ቤት ሠራተኝነት ተቅጥራ ለመስራት ነበር ስሚዝ ያለበት ከተማ በአንድ ወቅት ያቀናችው።
የእግዚአብሔር ሀሳብ ግን ሌላ ሆነና በመጀመሪያው ቀን ሳልቬሽን አርሚ በመጣችበት ጊዜ ላይ ጌታን ተቀበለች።
ስሚዝ እንደሚናገረው ፖሊን የወደፊት ሚስቱ እንደምትሆን በመጀመሪያ ያያት ቀን ነው የጌታ መንፈስ የመሰከረለት።
ስሚዝ የቧንቧ ሞያተኝነት ትምህርቱን በመማር ላይ እያለ በመንፈሳዊ ህይወቱ በቅርብ ሆኖ የሚረዳውና የሚከታተለው(mentor)
ሰው ጌታ አዘጋጅቶለት ነበር። ስሚዝ በኋላ ላይ ለደረሰበት ትልቅ መንፈሳዊ ከፍታ ይሄ ወንድም ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።
በተለይም ንጥቀትንና የጌታን ዳግመኛ መምጣት በተመለከተ ጠንካራ አቋም እንዲኖረው ጨብጥ አስይዞታል።
እንደዚህ መንፈሳዊ
ልጆችን በእውነት አምድ ላይ ተመስርተው የሚያሳድጉ አባቶች በዘመናችን ሁሉ አይጥፉ።
ስሚዝ በ19 አመቱ ሊቨር ፑል(liverpool )ወደምትባል ከተማ ሄደ። ፖሊንም ወደ ስኮትላንድ ሄደች። እሱም በሞያው የተዋጣለት የቧንቧ ሰራተኛ ሆነ። የሚያገኘውን ገቢ በአብዛኛው የሚጠቀምበት የጠፉትን ለመድረስ በተለይም የሚሰራው በወጣቶች ላይ ነበር
ከባድ የትውልድ ሸክም ነበረው።
በዚህም አገልግሎቱ ላይ የሚያግዘውን ሰው ጌታ ሰጥቶት ስለነበር ከዚህ አገልጋይጋ በአንድነት
ሆነው በሆስፒታል ያሉ ህመምተኞችን በየሳምንቱ በፆምና በፀሎት ሆነው እየሄዱ ያገለግሏቸዋል ወደ ሀምሳ የሚሆኑትንም
በወቅቱ በነበረው መጓጓዣ አህያን በመጠቀም በየሳምንቱ ወደ ቤተክርስቲያን ያመጧቸዋል። ብዙዎችም በዚህ አጋጣሚ ጌታን
የመቀበል እድል አግኝተዋል ። በዛ እድሜው የወንጌል አደራ ምን እንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ጥርት ባለ ሁኔታ የገለፀለት አገልጋይ
ነበር።
ስሚዝ በ1882 ወደ ብራድተመለሰ። ፖሊን እዛው ስኮትላንድ ቆየች። እሷም በዛ ስፍራ ሆና በጣም ጌታን
ታገለግላለች። እግዚአብሔር በሷ ሂወት ከሰራው ታሪክ አንዱ አንድ በጣም ባሏ እየደበደበ የሚያስቸግራት አብራት የምታገለግል
እህት ነበረች። በዚህም ምክንያት ፖሊንና ጓደኛዋ አብረው ሸክማቸውን በጌታ ፊት ያቀርባሉ በፀሎትም ይተጋሉ።ታዲያ ይሄ
የሚያናድደው አስቸጋሪ ሰው አንድ ቀን እየፀለዩ ሲያገኛቸው ከሚስቱ አልፎ ፖሊንንም ሳይቀር ፀጉሯን እየጎተተ ከቤት
ሊያስወጣት ሲታገል ፖሊን ለዚህ ሰው ደህንነት በጣም አጥብቃ ወደ እግዚአብሔር ትጮህ ጀመር። ፍቃዱንም ለመፈፀም
የሚተጋው ጌታ ጸሎቷን ሰማ ሰውየውም ጌታን አገኘ ፓሊንም ብዙ ሳትቆይ ከዛ በኋላ ወደ ብራድፎርድ(bradford )ተመለሰች። በፊት
ላይ እንደተጠቀሰው ስሚዝ ገና በመጀመሪያው ቀን እንዳያት ነው ከጌታ የተሰጠችው እንደሆነ የተረዳው ግን በመሀል ተራርቀው
የተለያየ ቦታ ሆነው ነበር ጌታን የሚያገለግሉት። ወደተለያየ ቦታ የሄዱበትም ምክንያት ግንኙነታቸውን ይፋ
ለማድረግ ሁኔታው አስቸጋሪ ስለሆነ ነበር ተብሎ ይገመታል። ግን ሁለቱም ወደ ብራድፎርድ(Bradford)በተመለሱ ጊዜ በትዳር
ለመጣመር ወስነው በአውሮፓ አቆጣጠር Dec 4,1882 የጋብቻ ስነስርዓታቸውን ፈፀሙ። በዚህ ትዳር ውስጥ አንድ ሴት ልጅና አራት ወንድ
ልጆችን አፍርተዋል።
ስሚዝ የተነሳበትን የማይረሳ ለተቸገሩ ርህራሄ የተሞላ ሰው በመሆኑ ምክንያት ቀለል ያለ ኑሮን የሚወድ ቁሳቁስ የማያታልለው
ህይወቱን በሙሉ ለጌታ ሰጥቶ የሚያገለግል ሰው እንዲሆን ምክንያት ሆኖታል። ጥንዶቹም አብረው ማገልገል ጀመሩ።
ፓሊንበማስተማር ፀጋዋ ታገለግላለች ስሚዝ ደግሞ ለሰዎች የደህንነትና የፈውስ ፀሎትን ያደርጋል። ስሚዝ አንደበተ ርቱዕ አልነበረምና
በዚህ ክፍተቱ ፖሊን ነበረች የምትረዳው። ሌላ የሚያስገርመው ታሪክ ደግሞ ስሚዝ በልጅነቱ ትምህርት ቤት ገብቶ
የመማር እድል በማጣቱ ምክንያት መፃፍና ማንበብ አይችልም ነበር። ማንበብን ያስተማረችው ሚስቱ ነች። ለማገልገል
ከሚያስፈልጉት ነገሮች ብዙ ነገር የጎደለው ሰው ቢመስልም እንኳን ግን ከሁሉ የበለጠው የእግዚአብሔር ቅባት በሱ ላይ
በሃይል ይሰራ ነበር።
ሚስት ከእግዚአብሔር የምትሰጥ ረዳት ነች የተባለው የእግዚአብሔር ቃል በሂወታቸው ተተግብሮ የታየበት ትዳር ነበራቸው።
በ1883-1884 አካባቢ ሀይለኛ ክረምት ተነሳ በዚህ ምክንያትም የቧንቧ ሙያተኛ ስራ በጣም ተፈላጊ ሆነ ከዚህም
የተነሳ ስሚዝ ከቤተክርስቲያን አገልግሎቱ ይልቅ ወደ ሙያተኛነት አገልግሎቱ አደላ። ፖሊን ግን በዛው በነበራት መንፈሳዊ
ሙቀት ጌታን ማገልገል ቀጠለች።
መቼም ሰው ፍፁም አይደለምና ስሚዝ በመንፈሳዊ ሂወቱ ሲደክም የስጋው ድክመቶቹም
እየጎሉ ይታዩ ጀመር። አንዱም አስቸጋሪ ባህሪው ቁጠኛነት ነበር። ታዲያም ይሄ ባህሪዉ ትዳሩ ላይ ችግር መፍጠር ጀመረ።
ከስራ ደክሞት ሲመጣ ምግቡ ተዘጋጅቶ እንዲጠብቀው ይፈልጋል ያ ያልሆነ ቀን በጣም ይነጫነጫል ይቆጣል። ታዲያ አንድ
ቀን ፖሊን ከአገልግሎት ቆይታ ስትመጣ የፊተኛውን በር ሆነ ብሎ ቆለፈው። እሷም ዞራ በሗላ በር ከፍታ ገባች በዚህ ጊዜ
በጣም ተናዶ እኔ የአንቺ ጌታ ነኝ እኔ ቤት ገብቼ እንዴት አንቺ ታመሻለሽ ለምን እንዲህ አደርገሽ በቁጣ ሲላት እሷም
በተረጋጋ መንፈስ ሳቅ ብላ አንተ ባሌ ነህ ጌታዬ ግን ኢየሱስ ነው ትለዋለች።
ስሚዝ ለሁለት አመት አካባቢ ከአገልግሎት ርቆ
በቧንባ ስራ ላይ ነበር ትኩረቱን ያደረገው። በዚህም ምክንያት መንፈሳዊ ሂወቱ ሳያስበው ደክሞ ነበር በነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ
የስጋውን ድካም ጎሽሞ መግዛት ያቃተው ሰአት ነበር ። ሰው በሃይሉ አይበረታም እንደሚለው የእግዚአብሔር ቃል ጉልበትን
የምናገኘው መንፈሳችንም የስጋችንን ፍላጎት የሚጫነው ከመስቀሉ ስር ስንሆን ብቻ ነው ። 1ኛ ቆሮንቶስ 10 :12 የቆመ
ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ይላል ቃሉ። እሷ ደግሞ በአንፃሩ የጌታ ቅባት በዝቶላት እያገለገለች ነበር። ስለዚህም ለሱ
ቁጣ ምላሽን በቁጣ አትሰጥም ይልቁንም የባሏ ሁኔታ እንዲቀየር በፀሎት አብዝታ ትተጋ ነበር።
"ጠቢብ ሴት ቤቷን ትሠራለች፤ ተላላ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች።”
ምሳሌ 1 : 14
መልካም የሆነው ጌታም ስሚዝ ነገሮችን ቆም ብሎ እንዲያስብና እንዲያስተውል የዛንው ቀን የልቦና አይኖቹን ከፈተለት። ከዛም
ለአስር ቀን ከጌታጋ የፅሞና ጊዜ ወሰደ ጌታም ሰርቶና አበጃጅቶ እንደገና ለክብሩ አቆመው ከዚያ ጊዜ ወዲህ ከሚስቱም
ከጌታውምጋ ተስማምቶ አገልግሎቱን ቀጠለ። ሰይጣን አፈረ እግዚአብሔር ከበረ። እግዚአብሔርን ለማገልገል ያለውም ጥማት
እየጨመረ ሄደ። 1897 አካባቢ የመለኮታዊ ፈውስ እንቅስቃሴ ጆን አሌክሳንደር ዳዊ (John alexander dowie )በሚባል ሰው ይካሄድ
ነበር። ስሚዝ እዛ ቦታ ላይ የጌታ እጅ በሀይለኛው ሲሰራ ሰዎች ሲፈወሱ ሲያይ የሱም አገልግሎት ወደዚህ እንዲያዘነብል
አጥብቆ መፀለይ ጀመረ። ሚስቱ ፖሊን በዚህ ሰው አገልግሎት ፈውስ ከተቀበሉት አንዷ ነበረች። ስሚዝ በራሱም ቤተክርስቲያን
ይህንን አገልግሎት መለማመድ ጀመረ። የጤና እክል ያለባቸውን ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሰብስቦ በማምጣት ይፀልያል ሰዎችም
በሚያስደንቅ ሁኔታ ይፈወሱ ጀመር።
በፈውስ ዙሪያ ቤተክርስቲያናቸው እውቅናን እያገኘ ሄደ በዚህም ምክንያት ብዙ በሽተኞች ፈውስን ፍለጋ ይመጣሉ
ፈውሳቸውንም ተቀብለው ይሄዳሉ። ስሚዝ የተፈወሱትን ሰዎች ምስክርነት እንዲሰጡ ያደርጋቸዋል በዛም ምክንያት ለፈውስ
የሚመጡት ቁጥር የበለጠ እየጨመረ ሄደ።
የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው እንዲሉ ስሚዝ በሆድ ድርቀት በሽታ ይሰቃይ ስለነበር ለዚህም በሽታ መድሃኒት ይወስዳል። አንድ
ቀን ሚስቱ እግዚአብሔር ይፈውሳል ብሎ የሚያምን ሰው መድሃኒት መውሰድ አለበት ወይ የሚል ጥያቄ አቀረበች እሱም ይሄ
እሱን እንደሚመለከተው ስለገባው ከዛ ቀን ወዲህ መድሀኒት መውሰድ አቆመ። መለኮታዊ ፈውሱንም ለአንዴና ለመጨረሻ
ተቀበለ። ከዚህም በላይ ከከፋ በሽታ ጌታ ፈውሶታል።
ታሪኩ እንዲህ ነው ...የትርፍ አንጀት በሽታ ነበረው። አንድ ማለዳ ላይ
በጠና ይታመማል ዶክተርም ተጠርቶ ይመጣና ከመረመረው በኋላ ይሄ በሽታ ለሂወቱ የሚያሰጋ ነው የሚል አሳዛኝ ሪፖርት
ለባልና ለሚስት ይነግራቸዋል። ሁለቱም አዝነው ተቀምጠው እያለ ሁለት አገልጋዮች ወደቤታቸው ይመጣሉ እነዛም ሰዎች
ፀልየውለት ሄዱ። ከዛም ስሚዝ ጠዋት ላይ እንደተለመደው ተነስቶ ለባብሶ ስታየው ሚስቱ ደንግጣ የት ልትሄድ ነው ስትለው
ተፈውሻለሁ ስራ መሄዴ ነው ብሏት ወጣ። እሱ እንደወጣ ተስፋ እንደሌለው የተናገረው ዶክተር መጣ ፖሊንም ቤት የለም
ወጥቷሎ ስትለው ዛሬ ባልሽ በሂወት አይመለስም ብሏት ሄደ። ስሚዝ ግን ከዛ በኋላ ለረጅም አመታት በጤና ጌታን
አገልግሏል። እሱ በዛ መከራ ያለፈው ለሌሎች እንዲራራና እንዲያፅናና እንደ ሆነ ያምናል። የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው
ማለት ነው። “እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን
ሁሉ ያጽናናናል።”2 ቆሮንቶስ 4:1
ለሰዎች ፈውስ በሚፀልይበት ጊዜ ለውጥ ካላየ ለሰአታት ፀሎቱን ይቀጥላል። በእግዚአብሔር ላይ ያለው እምነት በጣም ጥልቅ
ነበር። በሱ አገልግሎት ከሞት የተነሱ ሰዎች ሁሉ እንዳሉ ይነገራል።
የእግዚአብሔርን መንፈሳዊ ስጦታ ሁልጊዜ በጉጉት የሚጠባበቀው ስሚዝ በአሱዛ ስትሪት (Asuza street rivival 1906)
በተደረገው የማነቃቂያ ስብሰባ ላይ ተገኘ። በዛም ቀን ትኩረት ተሰጥቶ የሚፀለይበት ነገር በልሳን መሞላት ነበር። ስሚዝ ግን
እንደፈለገው በዛን ቀን አልሆነለትም። ግን ከዛ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በግሉ ተፀልዮለት በልሳን የመናገር ስጦታን አግኝቷል። ይሄ
መንፈሳዊ ስጦታ ከተጨመረለት በኋላ ሌላ አዲስ ምእራፍ በአገልግሎቱ ላይ ተከፈተ። ስሚዝ በመዝሙር የማስመለክና የፈውስ
ስጦታ ነበረው እንጂ ሰባኪ አልነበረም። በሰባኪነት የምታገለግለው ሚስቱ ነበረች። በአንድ ወቅት እሱ አገልግሎት ላይ እያለ ፖሊን በድንገት
በልብ ድካም እንዳረፈች ይነገረዋል። በፍጥነት መጥቶ መፀለይ ጀመረ ከዛም ነቃች ግን ጌታ ይፈልገኛል ስትለው ጌታ ከፈለገሽ
እኔ አልይዝሽም ይላታል። እሳም የምድር ሩጫዋን ጨርሳ ወደ ጌታ ተሰበሰበች። ነገር ግን ስሚዝ ሚስቱ በሞት ከተለየችው
በኋላ በጣም ህይወቱ መራራ ሆኖበት ስለነበር ወደ እሷ መቃብር መሄድን ያዘወትራል ። ማገልገል እስኪያቅተው ድረስ ልቡ
ተሰብሮ ነበር። ታዲያ አንድ ቀን እንደለመደው በመቃብሩ ስፍራ ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገር ጀመር እንዲህም ብሎ
ጌታን ተማፀነው እኔ ከዚህ በኋላ ማገልገል የምችለው የሚስቴን ፀጋ እኔ ላይ ከደረብክልኝ ነው። እግዚአብሔርም ፀሎቱን
ሰምቶ ከሀዘኑም አፅናንቶት በእጥፍ ቅባት ቀብቶት አገልግሎቱን መቀጠል ችሏል። በእርግጥ ሚስቱ ከጌታ የተሰጠችው ትልቅ
ስጦታ በአገልግሎቱም ላይ ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረገች ድንቅ የእግዚአብሔር ሴት ነበረች። ካሳለፋቸው ሁሉ ፈተናዎች ሚስቱን
ማጣቱ የከፋው ነበር። ፃድቅና ሩህሩህ የሆነው ጌታ ግን አጠገቡ ቆሞ አበረታው። ከዛም የተነሳ ለትውልድ የሚሻገርን ስራ
የመስራት አቅምን አግኝቶ በጣም ብዙ አገሮች እየሄደ አገልግሏል።
በአገልግሎቱ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆነበት ዋነኛው ምክንያት በአጠገቡ የነበሩት እንደተናገሩት ከእግዚአብሔርጋ የነበረው ጥብቅ
ግንኙነት ነው። ከሃያ ደቂቃ በላይ ሳይፀልይና ቃሉን ሳያነብ አይቆይም። የእግዚአብሔርን ቃል ከማንበብና ከመፀለይ ውጭ
ለሌላ ነገር ጊዜና ፍላጎት የለውም። አንድ ጊዜ ስሚዝ ሲያገለግል ያየውን ወጣት ልጅ በውስጡ ያለውን ፀጋ ለማነቃቃት ወደቤቱ
እንዲመጣ ይጋብዘዋል። ልጁን በር ሲከፍትለት ወጣቱ እንግዳው በአንድ እጁ ጋዜጣ መያዙን አየ። እሱም ይህ ውሸት የሞላበት
ፅሁፍ ወደቤቴ አይገባም ብሎ እንግዳውን ጋዜጣው ውጭ እንዲያስቀምጠው አድርጓል።
እንደዚህ የሚል መርህ ነበረው። "ከውስጣችንጋ እስኪዋሀድ ድረስ ቃሉን ማንበብ ከዛም ማመንና መተግበር"።
ሰዎች መፅሀፍ
ቅዱስን በግሪክኛና በዕብራይስጥ ያነባሉ እኔ ግን በመንፈስ ቅዱስ ነው የማነበው ይላል።
ስሚዝ የበሽታ ሁሉ ምንጩ ሰይጣን ነው ብሎ ያምን ስለነበር ለበሽተኞች ሲፀልይ አንዱ የሚያደርገው ነገር ህመሙ ባለበት
ስፍራ ላይ ይመታቸዋል። በዚህም ጉዳይ ሲወቀስ የሰጠው ምላሽ እኔ የምመታው ሰዎችን ሳይሆን በውስጣቸው ሆኖ
የሚያሰቃያቸውን አጋንንት ነው ለሱም ርህራሄ ሊኖረን አይገባም ይላል። አንድ ቀን በህክምናው አለም ተስፋ የተቆረጠበትን
ሰው ወደሱ ቤተክርስቲያን አመጡት ያ ሰው በበሽታ የተጎሳቆለና አቅም ያጣ ነው። ስሚዝ እንደተለመደው ያን ሰው በሚያመው
ቦታ ላይ በሃይል ይመታዋል እሱም ይወድቃል ያመጡት ሰዎች በጣም ይበሳጫሉ በቃ ገድለሀዋል እንከስሃለን ይሉታል። እሱ
ግን ምንም አልተደናገጠም አገልግሎቱን ቀጠለ ያም ሰው ተፈወሰ። ምንም እንኳን ጌታ በሱ አልፎ ለብዙዎች ፈውስ
ቢጠቀምበትም ግን ሁሉም የየራሱ መስቀል አለውና ሴት ልጁ መስማት የተሳናት ነበረች ግን ከባለቤቱ ሞት በኃላና
በዕድሜውም እየገፋ ሲሄድ በሚያገለግልበት ቦታ ሁሉ እሷና ባሏ አብረውት በመሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ ይረዱት ነበር።
እነሱም አፍሪካ በሚሽነሪነት ያገለግሉ ነበር። ስሚዝ በተለይ ባለቤቱ ወደ ጌታ ከተሰበሰበች በኋላ ጌታ በአስገራሚ ሁኔታ በፊት
በሷ በኩል የሚሸፍነው ጉድለቱ ተገፎ በድርብ ፀጋ በብዙ ስፍራዎች በመዟዟር በአስደናቂ ሁኔታ ጌታን አገልግሎ አስከብሮ